Site icon ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ከመምህራንና ሠራተኞች የተሰበሰበውን 1,682,504.71/አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰማንያ ሁለት ሺህ አምስት መቶ አራት ብር ከሰባ አንድ ሣንቲም / በዛሬው ዕለት በጦር ሀይሎች መከላከያ ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ በመገኘት ድጋፉን አስረክቧል።

ዩኒቨርሲቲውን በመወከል የገንዘብ ድጋፉን ያስረከቡት የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር ኡጁሉ ኡኮክ ሲሆኑ በንግግራቸው “ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን ሀገራዊ ጥሪውን ተከትሎ የተጣለበትን ሀላፊነት ለመወጣት ከመምህራን፣ ከሠራተኞችና ከዩኒቨርሲቲው የተሰበሰበውን ብር 1,682,504.71 ድጋፍ ለማስረከብ እዚህ ተገኝተናል ብለዋል።

ድጋፉን የተረከቡት በመከላከያ ሚኒስቴር የፋይናንስ ስራ አመራር ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ ወ/ሮ ማርታ ሎጂ በበኩላቸው “ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሠራዊቱን ለመደገፍ እያሳየ ያለው ርብርብ ትልቅ ውግንና ነው። ይህም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።

ሀገራችን ሁሌም ሰላሟን ለማስጠበቅ ጋምቤላም የዩኒቨርሲቲውን ሰላም፣ የአካባቢውን ልማት፣ የህብረተሰቡን ሰላም እንደሀገርም ተቀናጅተን ሰላም እንድናመጣ፤ የመማር ማስተማር ሂደቱም በተለይም ተማሪዎች በቀጣይ ሀገር ሰላም እንድትሆን የሚሰሩ ዜጎች እንደመሆናቸው መጠን በዚህ ተጠናክረው እንዲሰሩ ጥሪየን አስተላልፋለሁ። ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ላደረገው ድጋፍ በመከላከያ ሚኒስቴር ስም እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ ብለዋል።”

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀደም በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ለአማራና ለአፋር ክልል ወገኖች የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

Exit mobile version