አርእስተ ዜና
Tue. Apr 23rd, 2024

ዩኒቨርስቲዎች ከ91 ሚሊየን ብር በላይ ለገበታ ለሀገር አበረከቱ

Sep24,2020
ዩኒቨርስቲዎች ከ91 ሚሊየን ብር በላይ ለገበታ ለሀገር አበረከቱዩኒቨርስቲዎች ከ91 ሚሊየን ብር በላይ ለገበታ ለሀገር አበረከቱ

ከመስከረም 10 እስከ መስከረም 12 ቀን 2012 ዓ.ም በጅማ ዩኒቨርስቲ መሰብቢያ አዳራሽ ሲካሄድ የነበረው የከፍተኛ ትምህርት ማስቀጠያ ቅድመ ዝግጅት እና የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምላሽ ተግባራት አፈፃፀም ግምገማውን አጠናቋል፡፡

በማጠቃለያው ውይይት ዩኒቨርስቲዎቹ ለገበታ ለአገር ፕሮጀክት 91.3 ሚሊየን በገንዘብ፣24 ሚሊየን በአይነትና በሙያ እንዲሁም በጎርፍ ለተጎዱ ወገኖች 14.35 ሚሊየን በገንዘብና 1.1 ሚሊየን በአይነት ለማበርከት ቃል ገብተዋል፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በድጋፉ ተሳትፎ ያደረጉት 32 ዩኒቨርስቲዎች ናቸው፡፡

ፕሮጀክቱ በአዲስ አበባ ከተመረቁት በተጨማሪ በጎርጎራ፣ ወንጪ እና ኮይሻ ደቡብ ኮንታ ልዩ ወረዳ ውስጥ እንዲስፋፋ እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል፡ዩኒቨርስቲዎቹ በጎርፍ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖችም ከ14 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ጨምሮ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ፣ የከፍተኛ ትምህርት ስትራቴጂ ማዕከል፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ እና ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለዚሁ ዓላማ እንዲውል መስጠታቸው ይታወሳል፡፡
(ምንጭ ፡- የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር)

Related Post