Site icon ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ

የኢትዮ – አሜሪካን ኩባንያ ለግብርና ስራዉ ማስፋፍያ ባለሃብቶችን ጋበዘ

የኢትዮ - አሜሪካን ኩባንያ ለግብርና ስራዉ ማስፋፍያ ባለሃብቶችን ጋበዘ

የኢትዮ - አሜሪካን ኩባንያ ለግብርና ስራዉ ማስፋፍያ ባለሃብቶችን ጋበዘ

ኢታምኮ የተባለዉ የኢትዮ – አሜሪካን ኩባንያ በኦሮሚያ ክልል እያከናወነ ባለዉ የግብርና ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት ባለሃብቶች አብረዉት እንዲሰሩ ጥሪ አቀረበ።

አቶ ከበደ ጋሻዉ በካሊፎርኒያ ግዛት ወደ 45 አመታት ያህል በግብርና ስራ ላይ ተሰማርተዉ የሰሩ ሲሆን ከዛም ለብዙ አመታት ያካበቱዋቸዉን ልምድ ይዘዉ በሃገራቸዉ የግብርና ስራ ላይ ተሰማሩ ድርጅቱ ኢታምኮ ይባላል አቶ ከበደ ጋሻዉ አብራርተዉዋል።
[embedyt] https://www.youtube.com/watch?v=WDxIB50S3nw[/embedyt]
ድርጅቱም በዋነኝነት የተሰማራበትን የስራ ዘርፎች ምን ምን እንደሆነ ለኒዉ ቢዝነስ ኢትዮጲያ ገልጸዉልናል፣ ኢታምኮ ድርጅቱን በተለያየ ዘርፍ ለማሳደግ እቅድ ስላለዉ ለዉስጥም ለዉጪ ሃገር ኢንቨስተሮች ወይም ድርጅቶች ክፍት የሆነባቸዉን ሁለት ዋና ሴክተሮች ገልጸዉልናል። በአንደኛ ደረጃ ችግኝ የማፍላት ሴክተር ሲሆን ግሪን ሃዉስ የተሰኘ የችግኝ ማፍያ ዘዴን በመጠቀም ከአጋር ድርጅቶች ጋር የመስራት እቅድ አላችዉ። በሁለተኛ ደረጃ የአሳ ምርትን የተመለከተ ነዉ።

ኢታምኮ በሙሉ አቅሙ እንዲንቀሳቀስ የጸጥታ ጉዳይ እንዲስተካከል ፣ የባንክ ብድር በወቅቱ እንዲመቻችላችዉ እንዲሁም መጉላላትን እንዲቀንስ በመጭረስሻም የታክስ ስርአቱ ላይ ማሻሻያ ቢደረግ ለዉጥ ፈጣሪ ነዉ ሲሉ አቶ ከበደ ጋሻዉ ገልጸዋል።

Exit mobile version