Site icon ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ

ከ446 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች ሥራ ማቆማቸው ተገለጸ

ከ446 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች ሥራ ማቆማቸው ተገለጸ

ከ446 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች ሥራ ማቆማቸው ተገለጸ

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በክልሎች ደረጃ እየተካሄደ በሚገኘው “ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅንቄ ከ446 በላይ ኢንዱስትሪዎች ሥራ ማቆማቸውን መለየት መቻሉን ገለጸ፡፡

በክልሎች ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘው “ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ ሚያዝያ 29 እንደሚካሄድ ሚኒስቴሩ አስታውቋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በሰጡት መግለጫ የንቅንቄው ዋነኛ ዓላማ አምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ላይ ያሉ ችግሮችን ለመለየት፣ ሥራ ያቆሙ ኢንዱስትሪዎችን ለመለየትና ወደ ሥራ ለመመለስና አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ ነው ብለዋል።

ከዚህ አንፃር በክልሎች ደረጃ ሲካሄድ የቆየው “ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ችግሮችን ከመለየት አንፃር ውጤት እንደተገኘበትም ጠቅሰዋል። በንቅንቄው ከ446 በላይ ኢንዱስትሪዎች ሥራ ማቆማቸውን መለየት ተችሏልም ብለዋል።

ሚኒስትሩ የግብዓት፣ የፋይናንስ፣ የመሰረተ ልማት፣ ብቁ የሰው ኃይል እጥረትና የተቀናጀ የመንግሥት ድጋፍ አለመኖር ምርታማነትን ላይ እክል እንደፈጠረ የገለጹ ሲሆን 50 በመቶ የሆነውን የእምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ማሻሻል ሌላው አላማ ነው ብለዋል።

እነዚህን ችግሮች ለመፍታትም ንቅናቄው የአንድ ዓመት ብቻ ሳይሆን የረጅም ዓመታት ንቅናቄ በመሆኑ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ያስችላል ብለዋል።
በንቅናቄው የውይይት መድረክ፣ ኤግዝቢሽንና አርአያ የሚሆኑ አምራች ኢንዱስትሪዎችን እውቅና የመስጠትና ሌሎችም መርኃ ግብሮች ይኖሩታል ተብሏል።

Exit mobile version