Site icon ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በነሐሴ ወር ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል

ቅርንጫፍ ጽቤቱ በነሐሴ ወር ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል

ቅርንጫፍ ጽቤቱ በነሐሴ ወር ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል

በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በነሃሴ ወር ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ ፈቃደ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የስራ ሂደት አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች ጋር ባካሄዱት የ2015 በጀት ዓመት የነሐሴ ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማዊ ውይይት ወቅት እንደገለፁት በነሐሴ ወር ከቀጥታ ታክስ፣ ቀጥተኛ ካልሆኑ ታክሶችና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ብር 1ቢሊዮን 504ሚሊየን 227ሺ 818 ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 1ቢሊዮን 539ሚሊየን 613ሺ 220 በመሰብሰብ የእቅዱን 102.35 በመቶ ማሳካት መቻሉን ገልጸዋል፡፡

አፈፃፀሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ክንውን ጋር ሲነፃፀር በብር 437ሚሊየን 520ሺ 799 ወይም 44 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ገልፀዋል፡፡
አቶ ያሬድ አክለውም 2015 በጀት ዓመት በዓመቱ ለመሰብሰብ ከተያዘው 33 ቢሊዮን ብር በላይ የምንሰበስብበት እና የሀገሪቱን ወጪ በሀገር ውስጥ ገቢ መሸፈን ተገቢ ነው የሚለውን የሚኒስቴር መስሪያቤቱን የ2022 ራዕይ እውን ለማድረግ መሠረት የምንጥልበት ዓመት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አቶ ያሬድ አያይዘውም ለዚህ ወር ስኬት ከፍተኛ ሚና ላበረከታችሁ የቅርንጫፋችን አመራርና ሰራተኞች እንዲሁም ግብራችሁን በወቅቱ ለምትከፍሉ ታማኝ ግብር ከፋዮች ምስጋና በማቅረብ በቀጣይ ወራቶች እስካሁን የነበሩንን ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠልና ክፍተቶቻችንን በመሙላት ተገልጋይ የሚመሰክሩለት፣ ለተገልጋዮች የምንሰጠው አገልግሎት ከሙስናና ከብልሹ አሠራር በፀዳ መልኩ ሆኖ ከእቅዳችን በላይ በመሠብሰብ ስኬታችንን ማስቀጠል ይገባናል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

Exit mobile version