አርእስተ ዜና
Tue. Apr 16th, 2024

ለእነሱም 1.2 ሚሊየን ብር የሚያወጣ እርዳታ ለግሶ ዘመቻውን አጠናቀቀ

Jul21,2020
ለእነሱም 1.2 ሚሊየን ብር የሚያወጣ እርዳታ ለግሶ ዘመቻውን አጠናቀቀለእነሱም 1.2 ሚሊየን ብር የሚያወጣ እርዳታ ለግሶ ዘመቻውን አጠናቀቀ

በ200 በተለያየ ሙያ ላይ በተሰማሩ በጎ ፈቃደኞች አማካኝነት ባለፉት 4 ወራት በአዲስ አበባ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ቤተሰቦችን, አቅመ ደካመሞችን, አካል ጉዳተኞችን እና ተጋላጭ ህመምተኞችን ለመርዳት ታስቦ የተጀመረው ለእነሱም የተሰኘው ዘመቻ ከ1.2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ዕርዳታን በመለገስ ተጠናቀቀ፡፡

ለእነሱም ዘመቻ በዚህም በ9 የአዲስ አበባ ክፍለከተሞች የሚገኙ ከ1000 በላይ የተቸገሩ ቤተሶቦችን ተጠቃሚ ማደረጉንና ከዚህ በላይ ግለሰቦች መርዳት መቻሉ በመዝግያ ስነስርዓቱ ላይ ተገለፃል፡፡ እገዛው ከተደረገላቸው መካከልም ሌሎችን በሚረዱበት ወቅት ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ በመሆናቸው በተለያዩ የለይቶ ማቆያ ያልሆኑ ሆስፒታሎች ውስጥ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ይገኙበታል፡፡

በዘመቻው መዝግያ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የጤና ጥበቃ ሚንስቴር የCOVID-19 አማካሪና በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሃኪም የሆኑት ዶ/ር አስቻለው አሻጋሪ ሲናገሩም ትልቁ ነገር በበጎ ፈቃድ ተነሳስቶ እርስ በእርስ መረዳዳት ሲሆን ይሄም ትልቅ ውጤት ሊመጣ እንደሚችል መማር የምንችልበት ዘመቻ ነበር ብለዋል፡፡

የቡድኑ አስተባባሪ የሆነችው ዕንቁ እስጥፋኖስ በበኩሏ በጎ ፈቃደኞቹ ሃገሪቷ በገጠማት የኮቪድ-19 ወረርሺኝ ለማገዝ ያሰቡ ጓደኛሞች በራስ ተነሳሽነት የጀመሩት እንደሆነ ገልፃ የተገኘው ውጤት ካቀዱትም በላይ መሆኑን አሳውቃለች፡፡ ለዚህም መሳካት ከጎናቸው የነበሩ ግለሰቦችንና ድርጅቶችን አመስግናለች::

ለእነሱም ብለን በአቅም ትንሽ ደካማ የሆኑ ወገኖችን ለመርዳት ስንነሳ የኮሮና ቫይረስ በመጀመሪያ በሃገራችን ሪፖርት ሲደረግ በቤታችን እንድንቆይ በመቻላችን የገቢ ምንጭ ለሌላቸው ለመድረስ ታስቦ የተጀመረ ነው ብላለች ወ/ሪት ዕንቁ ሲትናገር፡፡

በዚህ እርዳታ የንፅህና ዕቃዎች ምግቦችን እና በስተመጨረሻም ፍራሾችን በዘመቻው የተሰራጨ ሲሆን በቀጣይም ተመሳሳይ ሌሎች ስራዎችን ለማከናወን እንደሚሰሩ በየካ ክፍለ ከተማ በተካሄደው መዝግያ ፕሮግራም የነበሩ ተሳታፊዎች ገልፀዋል፡፡

Related Post