Site icon ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ

የአፍሪካና ሩሲያ የኢኮኖሚ ትብብር ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት በአዲስ አበባ ተከፈተ

የአፍሪካና ሩሲያ የኢኮኖሚ ትብብር ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት በአዲስ አበባ ተከፈተ

የአፍሪካና ሩሲያ የኢኮኖሚ ትብብር ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት በአዲስ አበባ ተከፈተ

የአፍሪካ እና የሩስያ የኢኮኖሚ ትብብር ማስተባበሪያ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት (አፍሮኮም) ጽህፈት ቤቱን በአዲስ አበባ ከፈተ፡፡

በመክፈቻ ስነ ስርአቱ ላይ የሩሲያ የፌደሬሽን ምክር ቤት አባል ሴናተር ኢጎር ሞሮዞቭ፣ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጀኒ ተረሂን እና የሃይማኖት አባቶችን የወከሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የበላይ ሃላፊ ብጹዕ አቡነ አረጋዊ እና የመንግስት ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ሴናተር ኢጎር እንዳሉት፥ ማዕከሉ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በንግድ እና በኢንቨስትመንት እና በተለያዩ የኢኮኖሚ መስኮች ለሚያደርጉት ግንኙነት የጎላ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል።

አምባሳደር ኤቭጀኒ ተረሒን በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሁለትዮሽ ግንኙነት ዘመናትን የተሻገረ ግንኙነት ቢኖራቸውም በንግዱና በኢኮኖሚው ዘርፍ የጎላ ትስስር ሳይፈጥሩ መቆየታቸውን ጠቁመዋል።

እንደ ኤፍቢሲ ዘገባ፤ የጽህፈት ቤቱ መከፈትም አገራቱ ለሚያደርጉት የንግድና የኢኮኖሚ ትብብር የመሰረት ድንጋይ ሆኖ ያገለግላል ነው ያሉት።

(ምንጭ – ኢ.ፕ.ድ)

Exit mobile version