Site icon ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ

የአአበባ ከተማ አስተዳዳር በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ድጋፍ አደረገ

የአአበባ ከተማ አስተዳዳር በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ድጋፍ አደረገ

የአአበባ ከተማ አስተዳዳር በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ድጋፍ አደረገ

የአአበባ ከተማ አስተዳዳር በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አደረገ።

አዲስ አበባ ከተማ የሁላችን ከተማ መሆንዋን በተለያዩ አካባቢዎች ለተከሰቱ የድርቅ አደጋዎች ድጋፍ በማድረግ አጋርነቱን ሁሌም በተግባር ያሳያል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ ለሁለተኛ ዙር የተደረገውን 22 መኪና የመኖ እና ለሠው የሚሆን የምግብ ፍጆታ የሚውል ቁሳቁስ ለክልሉ ፕሬዝዳንት ለሙስጠፌ መሃመድ አስረክበዋል።

በመጀመሪያ ዘር የአ/አበባ ከተማ አስተዳደር ለሱማሌ ክልል 100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ይታወሳል።

ከንቲባ አዳነች በሱማሌ ክልል የተከሰተው ድርቅ በሠው ህይወት ላይ ችግር እንዳይፈጥር ክልሉ ለሚያደርገው ጥረት ሁሌም ከጎናችሁ ነን ብለዋል።
የሱማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ባለፉት 3 ዓመታት በክልሉ ሠላምና ልማት በርካታ ለውጥ መመዝገቡን ገልፀው ዘንድሮ የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም ክልሉ የተለየ በጀት በመመደብ እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

ባለፉት 40 ዓመታት ያልታየ ድርቅ በክልሉ ተከስቷል ያሉት ሙሰጠፌ ችግሩን ለመቋቋም ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል። አቶ ሙስጠፌ መሃመድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሁለተኛ ዙር ለክልላችን ያደረገው ድጋፍ በክልሉ ህዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል ሲል የከንቲባ ጽፈት ቤት አስታውቋል።

(ምንጭ – ኢ.ፕ.ድ)

Exit mobile version