Site icon ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ

በኮንስትራክሽን የተሰማሩ ሁለት ድርጅቶች 780 ብር ሚሊዮን አስገቡ

በኮንስትራክሽን የተሰማሩ ሁለት ድርጅቶች 780 ብር ሚሊዮን አስገቡ

በኮንስትራክሽን የተሰማሩ ሁለት ድርጅቶች 780 ብር ሚሊዮን አስገቡ

በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ሥር የሚገኙ እና በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ሁለት የልማት ድርጅቶች ህዳር 15 እና 18 2013 ዓ.ም በተካሔዱ ውይይቶች ተገመገመ፡፡ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን እና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን 779.51 ብር ወይም የዕቅዳቸውን 94 በመቶ በሩብ ዓመቱ ማግኘት ችለዋል፡፡

በሩብ ዓመቱ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ብር 573.57 ሚሊዮን አጠቃላይ ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ብር 601.34 ሚሊዮን በማግኘት የዕቅዱን 105 በመቶ ማከናወን ችሏል፡፡ በዚሁ ጊዜ ውስጥ የብር 32.1 ሚሊዮን ኪሳራ እንደሚደርስበት አቅዶ ቢሆንም ባካሔደው አበረታች የለውጥ ሂደት የብር 96.54 ሚሊዮን ትርፍ አስመዝግቧል፡፡ በቀጣይም በተለይ በፕሮጀክት ረገድ ያሉበትን የአፈጻጸም ክፍተቶች ለመቅረፍ የሚያስችል የፕሮጀክት ማኔጅመንት ሪፎርም ዕቅድ በዕለቱ ግምገማ መድረክ ይፋ አድርጎ በሰነዱ ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ከኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ጋር ተፈራርመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን እና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ደግሞ በሩብ ዓመቱ ብር 255.66 ሚሊዮን የአገልግሎት ሽያጭ ገቢ ለማግኘት አቅዶ ብር 178.17 ሚሊዮን በማግኘት የዕቅዱን 70 በመቶ ማከናወን ችሏል፡፡ ከጠቅላላ ገቢውም ብር 48.63 ሚሊየን ትርፍ ከታክስ በፊት ለማግኘት አቅዶ ብር 49.58 ሚሊዮን በማገኘቱ አፈጻጸሙ 102 በመቶ ሆኗል፡፡ ከጠቅላላ ገቢው ውስጥ በውጭ ንግድ በሩብ ዓመቱ 81 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት አቅዶ 41 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ሊያገኝ ችሏል፡፡

እነዚህ ሁለት የኮንስትራክሽን ተቋማት በሩብ ዓመቱ ብር 829.23 ሚሊዮን አጠቃላይ ገቢ ለማግኘት ያቀዱ ሲሆን ብር 779.51 ወይም የዕቅዳቸውን 94 በመቶ ማግኘት ችለዋል፡፡
የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኃብታሙ ኃይለሚካኤል የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽንን የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም በመሩበት ወቅት ኮርፖሬሽኑ ከነበሩበት ተግዳሮቶች ወጥቶ ትርፋማ መሆን መቻሉ የሚያስመሰግነው እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

የመጀመሪያውንና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽንን ግምገማ መድረክ የመሩት አቶ ከበደ ገለታ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ዳይሬክተር ሲሆኑ፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ኃይለሚካኤል መርተውታል፡፡ በግምገማው የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እና ዘርፉን የሚከታተሉ የኤጀንሲው ባለሙያዎች ተካፍለዋል፡፡

በቀጣይም ኮርፖሬሽኑ የፈጠረውን መልካም የሥራ አካባቢ፣ የእኔነት ስሜት፣የፕሮጀክት አፈጻጸም ብቃት፣የወጪ ቁጠባ አሰራር እና የመናበብና በጋራ የመስራት እንዲሁም የለውጥ ትግበራ በማጠናከር መሥራት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል፡፡ የበለጠ ትኩረት ተሰጥቷቸው መተግበር ያለባቸውን ተግባራት ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽንን የመጀመሪያው ሩብ ኣመት የሥራ አፈጻጸም ከመገምገም በተጨማሪ የኤጀንሲው ከፍተኛ አመራሮች ኮርፖሬሽኑ የሥራ አካባበውን በተመለከተ እያካሄደ ያለውን ለውጥ ተዘዋውረው ገምግመዋል፡፡

Exit mobile version