በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ትናንት በድሬዳዋ ከተማ ባደረገው ክትትል በተለምዶ ሶስት ኪሎ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ እና 4 ነጥብ 1 ኪ.ግ የሚመዝን ‘አኳ ማራይን’ የተባለ ማዕድን በቁጥጥር ስር አውሏል።
ሕገወጥ አዘዋዋሪዎቹ ማዕድኑን ወደ ውጭ ሀገር ለማስወጣት እና ለመሸጥ በዝግጅት ላይ እንዳሉ በድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም በብሄራዊ መረጃ ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።
በሕግ ማስከበር ስራው የሀገር ሐብቱን ሲያዘዋውሩ የተገኙ አራት ተጠርጣዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፤ የተያዘው ማዕድንም በድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ ቀጣይ ምርመራ እየተካሄደበት ይገኛል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን በሕግ ማስከበር ዘመቻው ተሳትፎ ላደረጉ የድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች እንዲሁም ለፌደራል ፖሊስ አባላት ምስጋና አቅርቧል።
ምንጭ: የጉምሩክ ኮሚሽን