Site icon ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ

በህገ ወጥ መንገድ የተገኘ 50 ሺህ ሊትር የምግብ ዘይት ተያዘ

በህገ ወጥ መንገድ የተገኘ 50 ሺህ ሊትር የምግብ ዘይት ተያዘ

በህገ ወጥ መንገድ የተገኘ 50 ሺህ ሊትር የምግብ ዘይት ተያዘ

በህገ ወጥ መንገድ መጋዘን ውስጥ ሲራገፍ የተገኘ 50 ሺህ ሊትር የምግብ ዘይት በቁጥጥር ስር መዋሉን የሐረሪ ክልል ንግድ ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የምግብ ዘይቱ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- 29490ኢት ተሳቢ የጭነት ተሽከርካሪ በሐረር ከተማ ሃመሬሳ አካባቢ በሚገኝ አንድ መጋዘን ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ ሲያራግፍ መገኘቱን የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ቡሽራ አልይ ዛሬ ተናግረዋል።

መነሻውን ጅቡቲ ወደብ በማድረግ በአካባቢ ለማከፋፈል ታስቦ እንደነበር በተገኘው ማስረጃ መረጋገጡን አስረድተዋል። በጭነት ተሽከርካሪው ላይ ከነበረው ግማሽ ያህሉ የምግብ ዘይት ተራግፎ ወደ መጋዘን እንደገባና ቀሪው እንደተጫነ መገኘቱን ነው ሃላፊ ያስረዱት።



ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት ከሌሎች የህግ አስከባሪዎች ጋር በመሆን በተደረገው ክትትል በህገ ወጥ መንገድ የተገኘውን የምግብ ዘይት መቆጣጠር እንደተቻለ የገለጹት አቶ ቡሽራ፤አሽከርካሪው ለጊዜው ከአካባቢው መሰወሩን ጠቁመዋል።

በቁጥጥር ስር የዋለው ዘይትም የጽህፈት ቤቱ ማኔጅመንት ተወያይቶ በሚወስነው መሰረት ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚከፋፈል አስታውቀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

(ምንጭ – ኢ ፕ ድ)

Exit mobile version