Site icon ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ

ሙስናን እንዴት እንከላከል

ሙስናን እንዴት እንከላከል

ሙስናን እንዴት እንከላከል

በስንታየሁ ግርማ – ፕሮፌሰር ዩሪ ሀረሪ የአለም ማህረሰብ በጋራ መዋጋት ያለበት ሶስት ዋና ዋና ችግሮች የአየር ንብረት ለዉጥ፤የኑክሊየር ሀይል እና አርትፊሻል ኢንተለጀንሲ ጋርየተያያዙ አሉታዊ ችግሮች ናቸዉ፤፤በእኔ እምነት ግን ከዚህም የባሰ ችግር አለ እሱም ሙስና ነዉ፤፤ ለምሳሌ የአየር ንብረት ለዉጥ፤ለመቆቆም የሚመደብ ሃብት በሙስና ሊባክን ይችላል፡፡

ስለዚህ ሙስናን መከላከል ዋነኛ ተግባር መሆን አለበት፡፡መረጃወች እነደሚያሳዩት ከሆነ በሙስና በማድግ ያሉ ሀገሮች በያአመቱ 1.26 ትሪሊዮን ዶላር ያጣሉ፡፡አፍሪቃ በየአመቱ 50 ቢሊዮን ዶላር ታጣለች፡፤(ኒዉ ታየምስ፣2022). ኒዉ ታየምስ፣ አክሎም እኤአ በ 1980 እና በ2018 መካከል አፍሪቃ በኢንቨስተመንት እና በእርዳታ መልክ 2 ትሪሊዮን ሰታገኝ 1.3 ትሪሊዮን ዶላር በህግ ወጥ መልኩ ከአፍሪቃ ወጥቶል፡፡ይህ ገንዝብ ደግሞ 1.25 ዶላር በታች የሚያገኙ ድሆችን ከድህነት ወለል በታች ማዉጣት ይችላል ይላሉ ባለሙያወች፡፡ሙስና በአለም ላይ በአሁኑ ወቅት ቁጥር አንድ በሽታ ነዉ፡፡ የኮቪድ ክትባት እና መድሃንት እንኮን ለሙስና ምቹ ሁኔታ ዕየፈጠሩ ነዉ፡፤ስለዚህ ሙስናን መካላከል ቁልፍ ጉዳ ይ መሆን አለበት፡፡

የስነ ምግባር መበልጸግ ሙስናን ለመከላከል አይነተኛ ሚና አለዉ፡፡
በዚህ አለም እንደ ሥነምግባር በመጥፎም ሆነ በጥሩ ለሀገርም ሆነ ለተቋማት ወሳኝ ነገር የለም፡፡ በአለም ላይ ያደጉ እና የለሙ ሀገሮች መሠረታቸው ስነምግባር ነው፡፡ ለምሣሌ የምዕራቡ አለም እድገት “ከኘሮቴስታንት ስነ ምግባር” ጋር ሲያያዝ በ3ዐ አመታት ውስጥ ከግማሽ ቢሊዮን በላይ ህዝብ ከድህነነት ወለል በማውጣት የምትታወቀው ቻይና እድገት ጥቂት ኋላ ቀሪ የኮንፈሲየስ ባህላዊ እሰቶች ከመለወጥ እና አብዛኛዉን ከማበልጠግ ጋር ይያዛል፡፡ በአለም በከፍተኛ
ፍጥነት እድገት ያስመዘገቡ የሩቅ ምሥራቅ ኤስያ ሀገራት ደግሞ እድገታቸው ከህዝብ ብሔራዊ መግባባት ጋር ይያዛል፡፡

እንደኰሪያ የመሣሰሉት ሀገራት ሌባ እንኳን ለክቶ የሚሠርቅበት ሀገር ነበሩ፡፡ ለምሣሌ ለኤክስፖርት በተዘጋጀ ምርት እና አገልግሎት ላይ የጉምሩክ ሠራተኞች ስርቆት አይፈፅሙም ነበር፡፡ መሀንዲሶች በሚገነባው ጤና ጣቢያ፣ ትምህርት ቤት፣ መንገድ የራሳቸውን 1ዐ በመቶ ኮሚሽን በመጨመር በጥራቱ፣ በጊዜውናበመጠኑ ላይ አይደራደሩም ነበር፡፡

ይህንን እስቲ ከእኛ ጋር ሌቦች ጋር አወዳድሩት ከዚህ በመነሣት ሥነምግባር ሙስናን ለመከላከል ወይንም ለመከሠት ዓይነት ሚና እንዳለው መረዳት እንችላለን፡ማህበረሰቡ ከማንኛውም የመንግሥት ተቋም ፍትሃዊ፣ ቀልጣፋ፣ ትክክለኛ አገልግሎት ይጠብቃል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ደንበኛ ሁልጊዜ ትክከል ነው ሉዕላዊ” ነው የሚሉት አባባሎች ከመቸውም ጊዜ የበለጠ ይሁንታ እያገኙ ነው፡፡

ደንበኛ ለማርካት የማይጥር ድርጅት፣ ተቋም፣ ሀገር እራሱን በገመድ አንቆ እንደ መግደል እየታየ ነው፡፡ ምክንያቱም ደንበኛ/ተገልጋይ የሚያማልሉ አገልግሎት ሰጪዎች እንደ አሸን እየፈሉ እና የድንበር የለሽ እየሆኑ ነው፡፡

ምንም እንኳን በማህበረሰቡ ፍትሀዊ አገልግሎት ቢጠበቅም በማደግ ባሉ ሀገራት ግን ሥነምግባራዊ እሴቶች በመንግሥት አገልግሎት አሠጣጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሸረሸሩ ነው፡፡ ይህ የመንግሥት አገልግሎት አሠጣጥ መላሸቅ በዋነኝነት የሚገለፀው በሙስና መልክ ነው፡፡ ሙስና የህዝብ ስልጣን ለግል ጥቅም ወይም ትርፍ ማዋል ነው፡፡ ጉዳቱ ግን ዘርፈ ብዙ ነው፡፡

ሙስና ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና አካባቢያዊ ተፅዕኖዎች አሉት፡፡ በፖለቲካው መስክ ሙስና የህግ የበላይነት መሸርሸርእና ለዲሞክሪሲ ማበብ ትልቁ እንቅፋት ነው፡፡ ሙስና በተንሠራፋበት የሰዎች እንጂ የህግ የበላይነት በሌለበት ተቋማት አይገነቡም፡፡ ተቋማት ባልተገነቡበት ሁኔታ ደግሞ አካታች ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሥርዓት አይመሠረቱም፡፡ በተቋማት ያልታገዘ እድገት እና ልማት ዘላቂነት አይኖረውም፡፡

በዳበረ የዲሞክራሲ ባህል ባላቸው ሀገራት ሣይቀር ሙስና የመንግሥት ቢሮዎች፣ ተቋማት፣ መርሆዎች ላይ እምነት በማሣጣት የቅቡልነት ቀውስ ውስጥ ይከታል፡በማደግ ላይ ባሉ ሀገሮች ደግሞ የበለጠ ጉዳት ያደርሳል፡፡ ሙስና በተንሠራፋበት ሁኔታ እና ቦታ ተጠያቂነት እና ልጓም ያለው የፖለቲካ አመራር ማስፈን አይቻልም፡፡

በኢኮኖሚው መሰክ ሙስና የሀገር ሀብት እንዲወድም ያደርጋል፡፡ በአብዘኛው ውስን የሆነው የህዝብ ሀብት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸው/ለድሆች/ ከፍተኛ ባልሆኑ ኘሮጀክቶች ማለትም እንደ ግድቦች፣ የሃይል ማመንጨዎች፣ የቧንቧ መስመሮች፣ አስደናቂ ግን መሠረታዊ ያልሆኑ አገልግሎቶች ላይ እንዲውል ይደረጋል፡፡ ት/ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ መንገዶች፣ ውሃ ወደ ገጠር አካባቢ እንዳይስፋፋ ያደርጋል፡፡ ከሁሉም የከፋ ደግሞ ውድድሩን በመገደብ የነፃ ገበያ እንዳይስፋፋ ያደርጋል ኢንቨስትመንትም ያቀጭጫል፡፡

ሙስና በህብረተሰቡ ማህበራዊ ትስስር ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከሁሉም በላይ ነው፡፡ ህብረተሰቡ በፖለቲካ ሥርዓቱ ላይ ያለውን እምነት ያቀጭጫል፡፡ በተቋማት እና በፖለቲካ መርሆዎች ላይ ያለውን ተስፋ ያጨልመዋል፡፡ ቀድሞ በአገልጋይነት ደካማ የነበረው የሲቪል ሠርቪሱ ላይ ተስፋ መቁረጥ እና ግድሌሽነትን በተገልጋይ ስሜት ያሣድራል፡፡ ይህ ደግሞ በዲሞክራሲ በተመረጡ መሪሆዎች ሳይቀር ህሊና ቢስ በማድረግ የህዝቡን ሀብት ወደ ውጭ ሀገር እንዲያሸሹ ይረዳቸዋል፡፡ ጉቦ መጠየቅ እና መስጠት አፀያፊ ስነምግባር መሆኑ ቀርቶ የተለመደ እና ቅቡልነት ያለው መጥፎ ባህሪ ያደርገዋል፡፡

ጥሩ የአካባቢ ህግ አለመኖር ወይንም ቢኖርም ተግባራዊ አለመሆን የበለፀጉት ሀገራት በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ከፍተኛ የኢንዱስትሪ ብክለት እንዲያስከትሉ ረድቷቸዋል፡፡ የቆሸሸ እና ጊዜው ያለፈበት ምርት መጣያ አርገዋቸዋል፡፡ የዘላቂ ልማት መርህን ወደ ጐን በመተው የተፈጠሮ ሀብትን ያለጥንቃቄ እንዲመዘብሩ አስችሏቸዋል፡፡ ጥቅጥቅ ያሉ የተፈጥሮ ደኖች ተጨፍጭፈዋል፡፡ ብርቅዬ እንስሳዎች፣ ዝሆኖች ወዘተ.. ጭካኔ በሞላበት ሁኔታ ተገድለዋል፡፡ ታድነዋል፡፡ ዝርያቸው የጠፉ እንስሳትና እና እፅዋትመ አሉ፡፡ በበለፀጉት ሀገሮች ብድርና ድጐማ አከባቢን አውደዊ ኘሮጀክት በገንዘብ በኩል ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡ ምክንያቱም የህዝቡን የጋራ ንብረት ወደግል ኪስ ውስጥ ለማስገባት ቀላል መንገዶች ነው፡፡

“The tragedy of the common “የሚለው አባባል በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ተፈጥሮ ሀብት ላይ በግልፅና በፍጥነት እየተተገበረ ነው፡፡ ጉቦ መስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑ ሰዎች ከሀገራቸው ይሠደዳሉ፡፡ ብቃት ያላቸው፣ ቅንና ትሁት ዜጐች ሀገራቸውን ጥለው ይሠደዳሉ፡፡ የመንግሥት ተቋማት የአድርባዮች፣ የሌቦች እና የአቅመ ቢሶች ስብስብ ይሆናል፡፡ ሀገርም ተወዳዳሪ መሆን አትችልም፡፡

ምንም እንኳን ሙስና በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በአካባቢ የሚያስከትለው ተፅዕኖ ለማሣየት ቢሞከርም ሙስና የሚያስከትለው ጉዳት ሊለካ አይችልም የሚሉም አሉ፡፡ በመጀመሪያ በሙስና መልክ የሚሠጠው ገንዘብ በመንግሥት የሂሣብ አያያዝ ሥራዓት ውስጥ አይመዘገብም፡፡ በየአመቱ ለሙሰኞች ሀላፊዎች እና ሠራተኞች የሚሠጠው ገንዘብ /ስጦታ/ ማንም ሊያውቀው አይችልም፡፡ ሙስና ገንዘብ ብቻ ሣይሆን ደግሞ በውለታ ሊሠጥ ይችላል፡፡

የከፋው ደግሞ የሙስና ማህበራዊ ጉዳቱ ሊለካ አይችልም፡፡ ብቁ መሀንድስ፣ እውቅና ያለው ሳይንቲሰት ሥራ ፈጣሪ ባለሀብቶችን ማጣት ሀገርን ምን ያህል እንደሚያስከፍል ማንም በቁጥር ማስቀመጥ አይችልም፡፡ በገንዘብ ከሚገመተው ውጭ በተጨማሪ በሙስና ምክንያት የሚፈጠረው መሃይመነት፣ ብቁ ባልሆኑ የህክምና አገልግሎት የሚፈጠረው የሰው ልጅ ነፍስ በስተጀርባ ያለውን የሰው ልጅ አሳዛኝ ሁኔታ መለካት አይቻልም፡፡ በአጠቃላይ የሙስና ወጪዎችን /ዝግጅት/ ለመለካት
የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ በግምት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡

የሙስና ዓይነቶች እና መገለጫዎቹም ብዙ ናቸው፡፡ ከነዚህም መካከል
 ጉቦ ወይንም ስጦታ መቀበል፣
 ለተሰጠ አገጀግሎት በክፍያ ወይንም በቴሌ መልኩ ከተገልጋዩ ምላሽ ማግኘት፣
 ሥራን በሚበድል መልኩ እና ሳያሣውቁ በአንድ ጊዜ ሁለት ቦታዎች መቀጠር፣
 ቅድመ ሁኔታዎች ላላሙሉ ድርጅቶች ወይንም ሰዎች በኮንትራት መስጠት፣
 አገልግሎትን ለማፋጠን ለአገልጋዩ የሚሠጥ ገንዘብ /መደለያ/፣

 የመንግሥት እቃ / አገልግሎት/ ከገበያ ዋጋ በታች መገመት፣
 ሀሰተኛ ሰነዶችን ማዘጋጀት፣
 በሥራ ላየ ለሌለ ሠራተኛ ደሞወዝ መክፈል፣
 የተለመደውን የመንግሥት አገልግሎት ለማግኘት የሚከፈል ክፍያ/ፈቃድ ለማውጣትና ለማደስ፣ የብቃት
ማረጋገጫ ለማግኘትና ለማደስ፣ ደብዳቤ ለመጻፍ ወዘተ../ ፣
 በእስር ላይ ያሉ ወንጀሎችን የእሰር ቤት ለማሣጠር /ለመልቀቅ/ የሚከፈል ክፍያ፣

 ላልተሰጠ አገልግሎት/ዕቃ/ ክፍያ መፈፀም፣
 ፋይሎችን መደበቅ፣
 በሥራ ምክንያት ያወቁትን መረጃ ለተወዳዳሪ መስጠት፣
የመንግሥት ሀበት እና ንብረት ለግል ጥቅም ማዋል፣
 ሌሎች የተሣሣተ ድርጊቶችን ለምሣሌ ግብር መሠወርና መደበቅ፣

መገለጫዎቹ ብዙ ናቸው፡፡ እንደየሀገሩ ባህልም ይለያያሉ፡፡ እነዚህ በአጠቃላይ የውቅያኖስ ውሃን በጭልፋ
እንደመጨለፍ ነው፡፡

የሙስና መንስኤዎች
ብዙ ባለሙያዎች የሙስና ዋነኛው መንስኤ የሞራል ዝቅጠት ነው ይላሉ፡፡ በተጨማሪም ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊ እና ተቋማዊ/የአስተዳደርና ቁጥጥር ድክመቶች/ እንደመንስኤነት ይጠቀሣሉ፡፡ ዘርዘር አድርገን ስናያቸው፡-
 ውጤታማ፣ ቁርጠኛ እና ስነምግባር የታላበሰ አመራር አለመኖር፣
 በመንግሥት ሃላፊዎች /ሠራተኞች/ ህጐች እና አሠራሮች መጣስ፣
 የፐብሊክ ሰርቪሱን ከመጠን በላይ ፖለቲካዊ ማድረግ፣
 ረቂቅ ህግ የማውጣት ስልጣን ያላቸው ተቋማት ህጉን ከህዝብ ጥቅም ይልቅ ለግል ጥቅም እንዲመች አድርጐ ማዘጋጀትና ማፅደቅ፣
 ስልጣን በአንድ ፖርቲ /ቡድን/በሞኖፖል ሲይያዝ፣

 የግል ተሣትፎ አነስተኛ ሲሆን፣
 አለምአቀፍ ተቀባይነት ያላቸው የፐብሊክ ሠርቪስ መርሆዎች/ግልፅ ጥናትና ተጠያቂነት/ መሸርሸር፣ መጥፋት፣
 ከፍተኛ የሥራ አጥ ቁጥር፣
 ጥልቅ የሆነ ድህነት፣
 ለፖለቲካ ፖርቲዎች የሚሠጥ ከፍተኛ ድጐማ፣

 የሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ ተቋማት ገለልተኛ አለመሆንና አለመጠናከር፣
 የመንግሥት ሠራተኛው የሥራ ዋስትና ማጣት፣
 ባህላዊ ልማዶች ለምሣሌ ለሀላፊዎች ስጦታ መስጠትና ማጐብደድ፣
 የስነ ምግባር ደንብ አለመኖርና ቢኖርም ተግባራዊ አለመሆን፣
 የከፍተኛ ሃለፊዎች የሀብት ምዝገባ/ትክክለኛነት በአግባቡ አለመረጋገጥ እና ህብረተሰቡን አለማሣተፍ፣
 ሙሰኞች ላይ የሚጣለው ቅጣት አስተማሪ አለመሆን፣
 ውስብስብ የእዝ ሰንሰለት መኖር፣
 በሥነ- ምግባር ላይ የሚሠጠው ስልጠና በቂ አለመሆን እና በውጤት አለመለካት፣

ሙስና እንዴት መቀነስ /መግታት/ይቻላል?
በአሁኑ ወቅት ሙስና በመላው አለም መነጋገሪያ ጉዳይ ነው፡፡ ሙስና በአለም ዙሪያ ያሉ ሕዝቦችን የልማት እና የአድገት እድሎችን የሚነፍግ በሽታ መሆኑ በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ በሀብታምና በድሀ መካከል እየሰፋ ለመጣው ልዩነት ዋነኛ መንስኤ ነው፡፡ ለድሀ ሀገሮች ወደ ከፋ ድህነት ውስጥ መግባት ዋነኛ መርዝ እና ጦስ ነው፡፡ ከዚህ በመነሣት ሙስናን ለመዋጋት በለሙያዎች የሚከተሉትን ይመክራሉ፡፡

 ሙስናን እና ህገወጥነትን ለመከላከል የሚያስችል የህግ ስርአቶችን መዘርጋት፣ የተዘረጉትን የህግ ስርዓቶች ለማስቀጠል የህግ አውጭና ተቋማዊ ማዕከሎችን ማስተካከል፣
 ባለሥጣኖች ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ሀብት እንዲያስመዘግቡ ማድረግ እና በሙስና ሲዘፈቁ ያለምህረት መቅጣት፣
 የዲሞክራሲ እና የሰብአዊ መብቶች ተቋማት በግልፅኝነትና በገለልተኛነት እንዲሠሩ መፍቀድ፣የፀረ ሙስና ከፍተና አመራሮች ምደባ በሜሪት ማድረግ
 በብድር እና በእርዳታ የሚገኝ ገንዘብ በጋራ ቁጥጥር የሚደረግበትን ሥርዓት ማዘርጋት፣

 ለፖለቲከኞች ዜጐችን የሚያረካ የአስተዳደር ዘይቤን በማስተዋወቅ እና በማበረታት ሰዎች ለህዝብ ጥቅም እንዲሰሩ አና የግል ሀላፊነታቸውን እንዲያውቁ ማድረግ፣
 ህዝብ ቅሬታውን የሚልፅበት ግልጽ ሥርዓት መዘርጋትእና ማበረታታት፣ በመገናኛ ብዙሃን ሥርዓትን ማስተዋወቅ፣
 አገልግሎት አሠጣጥን ያልተማከለ ማድረግ፣
 አገልግሎትን በቴክኖሎጂ ማዘመን፣

 በዘመናዊ የአመራር አሠራሮች እና መርሆዎች ላይ በመመስረት የግዥ ሂደትን ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ ማድረግ፣ እንዲሁም ጥብቅ ክትትል እና ቁጥጥር ማድረግ፣
 የስነ-ምግባር ደንብን በአሣታፊነት ማዘጋጀት በጥብቅ ተግባራዊ ማድረግና የማበረታቻ ሥርአት መዘርጋት፣
 ፖሊስንና የፍትህ ተቋማትን ማጠናከር፣
 ከሀገር ውጭ ሀብት የሚያሸሹትን አለምአቀፍ ማህበረሰብ እንዲወገዙ ማድረግ፣
 የሠራተኞችን ጥቅማ -ጥቅም ከግል ሴክተሩ ጋር ተወደዳሪ ማድረግና ከሌሎች ሀገሮች ልምድ መውሰድ፣ለምሣሌ ከሲንጋፖር

 ስነ-ምግባራዊ መሪዎችን ወደ ሀላፊነት ማምጣት/ብቃታቸውንና ባህሪያቸው የተመሠከረላቸው ሀላፊዎችን ብቻ መሾም፣
 የሠራተኞች እና የመሪዎች ውጤት ሲመዘን ለሥነ ምግባር ከፍተኛውን ከብደት መስጠት፣
 የምርመራ ጋዜጠኝነትን ማበረታት፣
 በሙስና መከላከል በአጭር ጊዜ ከፈተኛ ውጤት ካመጡት ሀገሮች ለምሣሌ ሲንጋፖር፣ ኢንደኔዥያ፣ ሆንግ
ኰንግ ልምድ መቅሰም፣
 የስነ ምግባር ኮሚሽን የመመርመር እና የመከሰስ ስልጣን ውጤታማ እንደሚያደርግ ከኢዶንኔሽያ መማር ይቻላል፡፡

ኢንዶኔዥያ፣ በአምስት አመታት ውስጥ በመቶ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን 1ዐዐ ኘርሰንት የጥፋተኝነት ውሣኔ እንዲሠጥባቸው አድርጓል፡፡ ብዙውን ጊዜ የመመርመርና የመከሰስ ስልጣን ለተለያዩ ተቋማት መስጠቱ የቅንጅቱ ችግር በመፍጠር የጥፋተኝነት ውሣኔ ምጣኔን ዝቅተኛ ያደርገዋል፡፡

 በከፍተኛ ሙስና ላይ የተዘፈቁትን በሞት ቅጣት ለመቅጣት ህጉን ማሻሻል፣
 የህብረሰቡን፣ የሰቪል ማህበራት፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ መገናኛ ብዙሃንን በማሣተፍ በሥነምግባር ግንባታ እና በሙስና መከላከል የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ማድረግ፣

 የመንግስት ሰራተኞችን ደመወዝና ጥቅማጥቅም ማሻሻል ለዚኅም በየጊዜዉ ከዋጋ ዉጣ ዉረድ ጋር እያጠና መፍትሄ የሚያቀርብ ቦርድ ማቆቆም፡፡ ወጣቶችን በጸረ ሙስና ፖሊሲ ቀረጻ እና ትግበራ ንቁ ተሳታፊ ማድረግ
 ሙስናን ብቻ የሚዳኝ የዳኝኘት ስረአት መመስረት
 በከፍተኛ ሙስና ላይ የተዘፈኩትን በሞት ለመቅጣት የህግ ማሻሻያ ማድረግ

Exit mobile version