Amharic Opinion

አዲስ አበባ ወይስ ጓንታናሞ…

በጌጡ ተመስገን – * ጠላት ሀገር እንኳን በዚህ መልኩ አይዘረፍም! ~ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ብርሃኑ ጸጋዬ
* አዲስ አበባ ውስጥ 7 ግፍ የሚፈፀምባቸው ድብቅ እስር ቤቶች ተገኙ
* የሰኔ 16ቱ የአዲስ አበባው የቦምብ ጥቃት የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት የቀድሞ ኃላፊ የተመራ ነው

***
« በአዲስ አበባ ዜጎች ከሰባት ወደማያንሱ ስውር ማሰቃያ ስፍራዎች ‘በአምቡላንስ እየተጓጓዙ!’ ኢ- ሰብአዊ ድርጊት ይፈጸምባቸው ነበር »

በእነዚህ እስር ቤቶች ዉስጥ

በኤሌከትሪክ ሽቦ መጥበስ፣ በጀርባ አስተኝቶ በአፍና አፍንጫ ላይ ፎጣ በማድረግ በውሃ ማፈን፣ ለረጅም ጊዜ ፀሐይ እንዳያገኙ ማድረግ፣ ዛፍ ላይ ሰቅሎ መግረፍ፣ ጥፍር መንቀል፣ ጫካ ውስጥ ራቁትን ማሳደር፣ ዘቅዝቆ መስቀል፣ ሙቀት ባለባቸው አካባቢዎች በሙቀት ማሰቃየት፣ አይንን ሸፍኖ ራቁትን ጫካ ውስጥ መጣል፣ አልፎ አልፎ ደግሞ ከአውሬ ጋር ማሰርን የመሰሉ ተግባሮች ሲፈፀሙ ነበር ።

በተጨማሪም ብልትን በፒንሳ መጎተትና መሳብ፣ ብልት ላይ ውሃ ማንጠልጠል እንዲሁም ሴቶችን እየተፈራረቁ መድፈርና ወንዶች ላይ የግብረ ሰዶም ድርጊት መፈጸም በእነዚህ እስር ቤቶች ይፈጸመ ነበር፡፡

***
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን በተመለከተ፦
ከ2004 እስከ 2010 ድረስ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን 37 ቢሊየን ብር የውጭ ግዢ ፈፅሟል።

እነዚህ ግዢዎች ዓለም አቀፍ ጨረታ ሳይፈፀምባቸው የተከናወኑ ናቸው።

ግዢዎቹ በጥቅም በተሳሰሩ ግለሰቦችና ተቋማት መካከል የተከናወነ ነው።

ከመደበኛው ዋጋ እስከ 400% ተጨማሪ ዋጋ እየተጨመሪ ግዢ ይፈፀም ነበር።

***
የሰኔ 16 ቱ የቦምብ ጥቃት የተቀናበረው በብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኦሮሞ ስለሆኑ በኦሮሞ ቢገደሉ ተብሎ ነው በሙከራው ኦሮሞዎች እንዲሳተፉ የተደረገው።

መቀመጫዋን ኬንያ ያደረገችውና በጥቃቱ ተባባሪ የሆነችው ገነት ወይም ቶለሽ የተባለችው ግለሰብም፥ በሰው ምልመላና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ተሳትፋለች።

***
ሜቴክ ከ2004-10 ዓ.ም ከ 37 ቢሊዬን (2.5 ቢሊዬን ዶላር) የውጭ ግዢ ያለጨረታ ከውኗል።

የሃገር ውስጥ ግዢ ሙሉ ለሙሉ ያለጨረታ ተከናውኗል።

የሀገር ውስጥ ግዢም በግልፅ ጨረታ መፈፀም ሲገባው እስካሁን በዚህ መልኩ የተፈፀመ የለም።

ከኮርፓሬሽኑ አመራሮች ጋር የዝምድናና የጥቅም ትስስር ካላቸው ሰዎች በብዙ እጥፍ በተጋነነ ዋጋ ይገዛ ነበር።

ከአንድ ድርጅት 21 ጊዜ፣ ከሌላው ደግሞ 15 ጊዜ ግጭ ተፈፅሟል።

ሜቴክ ከአንድ ተቋም ጋር ተደጋጋሚ ግዥ ይፈጽ ማል፤ለአብነት ያህል ከአንድ ድርጅት ብቻ የ205 ቢሊዮን ብር ግዥ ያለጨረታ ተፈጽሟል፤

***
ከተቋሙ ተልዕኮ ውጪ የተፈፀሙ ግዥዎችም አሉ። ከዚህም ውስጥ የመርከብ ግዢ ይገኝበታል። በማይመለከተውም ስራ ገብቶ ወደ ንግድ ስራ አስገብቷቸዋል

***
ሜቴክ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚንስትር ትእዛዝ አልቀበልም ብሏል፡፡

***

በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል 36 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል

***
በአጠቃላይ እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋሉ የሜቴክና ደህንነት አመራሮች ቁጥር 63 ሲሆን እስካሁንም ያልተያዙ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የተደበቁ አሉ።

***
የሰኔ 16ቱ የአዲስ አበባው የቦምብ ጥቃት የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት የቀድሞ ኃላፊ የተመራ ነው

***
የመረጃ ደህንነት ኃላፊው ማን እንደሆኑ እያወቃችሁ አታድርቁኝ ።

***
ወንጀለኛ የማንም ብሔር ተወካይ አይደለም፡፡

***

ቀድሞ የመርከብ ድርጅት ይባል የነበረው የአሁኑ የየባህር ትራንዚትና ሎጅስቲክ ድርጅት አባይ እና አንድነት የሚባሉ ከ28 አመት ባለይ ያገለገሉ መርከቦች ነበሩት።

እነዚህ መርከቦች በባለሙያ በማስጠናት ከዚህ መርከቦቹ አገልገሎት ላይ መቆየት የለባቸውም፤ ከቆዩ ከገቢያቸው ወጪያቸው ይበልጣል ስለተባለ እንዲሸጡ የስራ አመራር ቦርዱ ይወስናል።

በዚህ መነሻነት ገዥ ተፈልጎ አንድ የውጭ ድርጅት በሶስት ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ዶላር አንዷን መርከብ ለመግዛት ቀረበ።

ነገር ግን ለው ድርጅት ከሚሸጥ ሜቴክ ቆራርጦ ብረቱን ይጠቀምበት በሚል ድርጅቱ ባቀረበው ዋጋ መሰረት በሦስት ነጥብ 276 ቢሊዮን ብር ሜቴክ እንዲገዛው ይደረጋል።

ይሁን እንጂ ሜቴክ መርከቦቹን ቆራርጦ ብረቱን መጠቀም ትቶ መርከቦቹ አዋጭ አይደሉም የሚል ጥናት እያለ ወደ ንግድ ሥራ አስገብቷቸዋል።

ወደ ንግድ ስራ ከማስገባቱም በፊት መስከረም 15 ቀን 2005 ዓም የሜቴክ ሥራ አመራር ቦርድ ተሰብስቦ መርከቦቹ ጅቡቲ ወደብ ላይ ለረጅም ጊዜ ከቆዩና ተጨማሪ ወጭ ካስወጡ በኋላ ለጥገና ወደ ዱባይ ተልከዋል።

ለጥገናውክ ከኮርፖሬሽኑ 513 ሚሊዮን 837 ሺህ ብር ወጪ ተደርጎ መርከቦቹ እንዲጠገኑ ተደርጓል።

ጥገናውን የሚያከናውኑ ሰዎችን የሚያፈላልጉ ተብለው የተመረጡትም ሜቴክ ውስጠ ያሉ የድልለላ ሥራ የሚሰሩ ከተቋሙ ኃላፊዎች ጋር የስጋ ዝምድና ያላቸው ግለሰቦች ናቸው።

በመጨረሻም መርከቦቹ ተጠግነው ወጥተዋል ተብለው ወደ ንግድ ገብተዋል።

ነገር ግን የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ አድረገው መንቀሳቀስ ስለማይችሉ ለጥገና ብለው የተንቀሳቀሱበትን ፈቃድ ይዘው ከኢራን ወደ ሞቃዲሾ በማድረግ እሰከ 500 ሺህ ዶላር አካባቢ ይሰራሉ።

ያገንዘበ ግን ወደሜቴክ ያልገባበት ሁኔታ አለ። ሥራውም ቢሆን ህገወጥ ነው።

በመጨረሻ መርከቧ ሥራ መስራት እንደማትችልና ፈቃድ እንደማታገኝ ሲታወቅና ተቃውሞ ሲያጋጥማቸው መርከቧ በሁለት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ብረ ተሽጣለች።

***
ይሄ ግዥ የተፈጸመበት አላማ በራሱ ችግር የለበትም። “አገራዊ ፐሮጀክቶችን በአውሮፕላን ታግዞ ለመከታተል” በሚል ያለምንም ጨረታ ከአንድ የእስራኤል ኩባንያ በ11 ሚሊዮን 732 ሺህ 520 ብር ነው ግዥው የተፈጸመው።

ነገር ግን ወደ ንግድ መግባት አለብን ተብሎ ፈቃድ በማውጣት ለመስራት ተሞክሮ አልተሳካም።

አውሮፕላኖቹ ከ50 አመት በላይ ያገለገሉ፤ የሚጠቀሙት ነዳጅ እጅግ ውድ፣ የቴክኒክ ችግርም ያለባቸውና ጥቅም ላይ ሊውሉ የማይቸሉ ናቸው ተብለው አራቱ ተቀምጠዋል።
አንደኛው ግን እስካሁን የት እንዳለ አልታወቀም።

***
ምርመራው ከ5 ወር በላይ ፈጅቷል። የዚህ ምክንያቱም በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦችን አስረን ከማጣራት አጣርተን ለማሰር ስለሞከርን ነው። ማንንም ተጠርጣሪ ሳንይዝ ነው ያጣራንው።

***
በሙስና 27 ሰዎች፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ደግሞ 36 ሰዎች በአጠቃላይ ከ 63 በላይ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ነው በመግለጫው የተመለከተው፡፡

~ ( ከአቃቤ ሕግ መግለጫ)