ስለ የኢትዮጵያ የቆዳ ጫማዎች ከነጋዴዉ አንደበት

Spread the love

ኢትዮጵያ በአለም ደረጃ የታወቀ የቆዳ ምርት አላት። በዚህም ምርቷን ወደውጪ ከመላክ ባለፈ ሀገር ውስጥ ላሉ የተለያዩ ምርቶች ለይ ለተሰማሩ ድርጅቶች በማስረከብ በርካታ ለአመታት የቆዩ የአገር ውስጥ አምራች ድርጅቶችን አገልግሎት መስጠት እየተቻለ ቢሆንም ህብረተሰቡጋር ተቀባይ መሆን ከባድ ፈተና ሆኖ ቆይቷል።

ባሁኑ ግዜ የማህበራዊ ገፃቸውን በመጠቀምና በተለያዩ መንገድ ተቀባይነታቸውን እያሰፉ ይገኛሉ።በዚህም በርካታ የኢትዮጽያ ምርት ሻጮች ይገኛሉ “ሰቦ” የኢትዮጵያ የቆዳ ምርት መሸጫ ድርጅትም አንዱ ነው። መንግስ በሀገሪቱለይ ያለውን የዋጋ ንረት ማረጋጋት ቢችል ከዚህ የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንደሚችሉ አያይዘው ይገልፃሉ።

የቆዳ ኢንዱስትሪዎች ልማት ማህበር ከመንግስት ተቋማትና ከባንኮች ድጋፍ በማመቻቸት በተጨማሪ ሁኔታውን ለማስተካከል እየሰራ ይገኛል፡፡ በመዲናዋ በሚገኘው የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ዘመናዊ ሱቅ ለማግኘት ሥራውን ጀምሯል፡፡
[embedyt] https://www.youtube.com/watch?v=2ah3NF_O64o[/embedyt]
በ 50 ሚሊዮን ዶላር በሚገመት ኢንቬስትመንት የታቀደው የ 3 ሺ ካሬ ኪ.ሜ ሱቅ ጥራት ያለው የቆዳ ምርቶችን ከመላው አለም ለሚመጡ ተጓዦች ያቀርባል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል ፡፡ ማህበሩ በየአመቱ በአየር ማረፊያው የሚያልፉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተጓዦችን ገበያ በማግኘት ገቢውን ለማጠናከር እቅድ ይዟል፡፡