በ7 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚገመቱ 17 የአጋርነት ፕሮጀክቶች ይፋ ሆኑ
Amharic News

በ7 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚገመቱ 17 የአጋርነት ፕሮጀክቶች ይፋ ሆኑ

በ7 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚገመቱ በትራንስፖርትና ሀይል አቅርቦት ዘርፎች ያተከሩ 17 የመንግስትና የግል አጋርነት ፕሮጀክቶች ይፋ ሆኑ።

የኢትዮጵያ የመንግስትና የግል አጋርነት ዳይሬክቶሬት ጀነራል ጽህፈት ቤት ካፀደቃቸው 17 ፕሮጀክቶች መካከል 14ቱ በሀይል አቅርቦት ዘርፍ ሲሆኑ፥ ሶስቱ የትራንስፖርት ፕሮጀክቶች እንደሆኑ ተጠቁሟል።

የሀይል አቅርቦት ፕሮጀክቶችም፦

ገናሌ ዳዋ 5 የሀይል ማመንጫ ፦ 469 ሜጋ ዋት፦ በ793 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

ገናሌ ዳዋ 6የሀይል ማመንጫ ፦ 100 ሜጋ ዋት፦ በ387 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ፣

ጨሞጋ የዳ 1ና 2 የሀይል ማመንጫ፦ 280 ሜጋ ዋት፦ በ729 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

ሀሌሌ ዋራቤሳ የሀይል ማመንጫ፦ 424 ሜጋ ዋት ፦ በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

ዳቡስ የሀይል ማመንጫ፦ 798 ሜጋ ዋት፦ በ984 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

ጋድ የፀሀይ ሀይል ማመንጫ፦ 125 ሜጋ ዋት ፦ በ150 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

ዲቻቶ የፀሀይ ሀይል ማመንጫ፦ 125 ሜጋ ዋት ፦ በ150 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

መቐለ የፀሃይ ሀይል ማመንጫ፦ 100 ሜጋ ዋት ፦ በ120 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

ሁመራ የፀሃይ ሀይል ማመንጫ፦ 100 ሜጋ ዋት፦ በ120 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

ወለንጪቲ የፀሀይ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት፦ 150 ሜጋ ዋት፦ በ165 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

ዌራንሶ የሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት ፦ 150 ሜጋ ዋት፦ በ165 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

መተማ የፀሀይ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት፦ 125 ሜጋ ዋት፦ በ150 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

ሁርሶ የፀሃይ ሀይል ማንጫ ፕሮጀክት፦ 125 ሜጋ ዋት ፦ በ150 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

እንዲሁም በዚህ ዘርፍ የሀይል ማስተላለፊያና ጣቢያ ፕሮጀክት መካተቱ ተነግሯል።

ይፋ በሆነው የአጋርነት ፕሮጀክት በትራንስፖርት ዘርፉ የአዳማ አዋሽ 125 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ በ440 ሚሊየን ዶላር፣ አዋሽ ሚኤሶ 72 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ በ230 ሚሊየን ዶላር እና ከሚኤሶ ድሬደዋ 160 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ በ445 ሚሊየን ዶላር የሚገነቡ ሲሆን በዚህ ጨረታ ወጥቶላቸው ወደ ስራ ይገባሉ ተብሏል።

በተለዩት ፕሮጀክቶች ዙሪያ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን፥ በዚህ ዓመት ጨረታ ወጥቶባቸው ወደ ግንባታ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ የመንግስትና የግል አጋርነት ዳይሬክቶሬት ጀነራል ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ተሾመ ታፈሰ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታውቀዋል።

ዳይሬክተሩ በቀጣይም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይልና የመንገዶች ባለስልጣን የአዋጭነት ጥናት ሲያቀርብ የኢትዮጵያ የመንግስትና የግል አጋርነት ዳይሬክቶሬት ጀነራል ጽህፈት ቤት ቦርድ ከፈቀደ በኋላ ጨረታ ወጥቶ የግል ባለሃብቱ እንዲሳተፍ ይደረጋል ብለዋል።

(በኤፍ.ቢ.ሲ)