በኦሮሚያ 180 ትምህርት ቤቶች ስራ ጀመሩ

በኦሮሚያ 180 ትምህርት ቤቶች ስራ ጀመሩ

Amharic News

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች በ3 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ 180 ትምህርት ቤቶች ስራ መጀመራቸው ተገለፀ።

ትምህርት ቤቶቹ በክልሉ የተለያዩ ዞኖች የተገነቡ ሲሆን፥ የሁለተኛ ደረጃና የመሰናዶ ትምህርት ቤቶች መሆናቸውን የክልሉ የትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ አለማየሁ አሰፋ፥ መንግስት በክልሉ ያሉ የሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤቶችን ቁጥር ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል።

በዚህ መሰረትም በሰሜን ሸዋና በሌሎች የኦሮሚያ ዞኖች ከ3 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ የተገነቡ 180 የሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤቶችን ስራ መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በክልልሉ ያለውን የትምህርት ጥራት ለማሳደግ የክልሉ መንግስት በርካታ ስራዎች እያከናወነ መሆኑ ነው አስታውቀዋል።

እንደማሳያም በ100 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የፊቼ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግንባታ መጠናቀቁን ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡