የኢትዮጵያ ፕሬስ ከድጡ ወደ ማጡ እንዳይሆን

የኢትዮጵያ ፕሬስ ከድጡ ወደ ማጡ እንዳይሆን

የኢትዮጵያ ፕሬስ ከድጡ ወደ ማጡ እንዳይሆን

በባየልኝ ባይሳ – ደ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በህዋላ አስደናቂ ፖለቲካዊ ለውጦች እንደመጡ እሙን ነው፡፡ ይህን ለማሳለጥ እንዲቻልም በርካታ የመንግስት ድርጅቶች መዋቅራዊና የአመራር ለውጦች ተደርገዋል፡፡ ይህ እየተካሄደ ያለው ለውጥም ውጤታማነቱ በሄደት እንደሚታይ ይታመናል፡፡

ነገር ግንአዲስ የሚመጡ አመራሮች በተመደቡበት ስራ ውጤታማነታቸው ሊለካ ከሚችልባቸወ አንዱና ዋንኝው ቀደም ሲል በመስሪያቤቶች የተሰሩትን ስህተቶች በማረም እንዲሁም በሰራተኞች ለይ የተፈጸሙ በደሎችን በማስወገድ ሰራተኛው ለስራ ተነሳሽነቱ እንዲጨምር ማድረግ ነው፡፡

ከአራት ወራት በፊት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቀድሞ ዋና እና ምክትል ስራ አስኪያጆች ባሰዩት ድክመትና ድርጅቱን ለመምራት ባሳዩት ድክመት ለቦታው ብቁ አይደሉም ተብለው ከሀላፊነታቸው ተባርረው በአዲስ አመራሮች እንዲተኩ ተደርገዋል፡፡

አዲሶቹ አመራሮችም ስራቸውን የጀመሩት በቅድሚያ ሰራተኛውን በየክፍሉ በመሰብሰብ ስለ ተፈጸሙት በደሎችና ቅሬታዎች እንዲናገር በማድረግ ሲሆን በዋንኛነትም የሰራተኛው ቅሬታ በቅርቡ በመስሪያ ቤቱ ተደርጎ የነበረወ የስራ ድልድል ህግን ያልተከተለ እንደነበር ማለትም በድልድሉ ወቅት የፖሊሲ ጥያቄዎችን በተመለከተ የተሰጠው ነጥብ ማለትም ከ35 በመቶ የተባለው የፖሊሲ ጥያቄዎች በተባለውና በሰዎች አመለካከት ላይ ያነጣጠረ ነጥብ አሰጣጥ ህገ ወጥ እንደነበር ጠቅሰው ይህንንም የቀድሞው የቦርድ አባለት ትክክል እንደልነበር ማረጋገጫ መስጠታቸው የተጠቀሰ ሲሆን በዚህ መሰረት ቅሬታው እንዲስተካከል የሚል ነበር፡፡

በድልድሉም ሳቢያ ከ24 በላይ የሚሆኑ ሰራተኞች ቅሬታ አቅርበው ሰሚ ማጣታቸው ተገልጾአል፡፡

ከዚሁ ጋር አንዳንድ በሀላፊነት ቦታ የተመደቡ ሰዎች በውድድር ሳይሆን ያለ ውድድር እንደሆነ እንዳውም ከመንግስት ሰራተኞች የስራ ቅጥር ደንብን በመተላለፍ አላግባብ ቅጥር ሰለተፈጸመ ድርጊቱን የፈጸሙ ሰዎች በህግ እንዲጠየቁ የሚል ነበር፡፡

ከወራት በህዋላም የመስሪያ ቤቱ የቦርድ አባላትና ሰብሳቢው በመስሪያ ቤቱ ተገኝተው ከሰራተኛው ጋር ውይይት ሲካሄድ ሰራተኛው በተለይ በድልድሉ ወቅት የተፈጠረው ስህተት እንዲታረምና ቅሬታው እንዲፋቅ ጥያቄ ቢቀርብም የቦርዱ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ካሳሁን ጎፌ፡ የናንተን ቅሬታ ለማስተካከል ተብሎ እንደገና የመዋቅር ማስተካከያ ስለማይሰራ ድልድሉ እንደሚጸና ተናግረ ል፡፡

ይህም ቅሬታ አቅራቢ ሰራተኞችን እጅግ አሳዝኖአል፡፡ በአሁኑ ወቅት በከተማልማት በሚኒስቴር ደኤታነት የሚያገለግሉት አቶ ካሳሁን እዚሁ መስሪያ ቤት በህዝብ ግንኙነት ሙያ ሲሰሩ በሰራተኝነታቸው በደል ደርሶባቸው ስራቸውን ለቀው እንደነበር ይታወሳል ታዲያ ችግሩን እያወቁ የሰራተኛውን ጥያቄ አድበስብሰው ማለፋቸወ ጉዳዩን አስገራሚ ያደርገዋል፡፡

ከዚህ በተቃራኒው ያለ ውድድር የተቀጠሩትን ሰራተኞች በቦታቸው እንዲቀጥሉ ጭራሹንም የከፍተኛ ደረጃ እድገት እንዲያገኙ ተደርጎ ቀጥሎአል፡፡

ያለ ውድድር በመስሪያ ቤቱ የተቀጠሩ
1 ሞላ ምትኩ የውጭ ቁዋንቁዋዎች ዳይሬክተር አላግባብ ተቀጥሮ አንድ ደረጃ ያደገ
2 ፍቃዱ ከተማ የሀገር ውስጥ ቁዋንቁዋዎች ዳይሬክተር ያላግባብ ተቀጥሮ በሶስት አመት ውስጥ አራት የሀላፊነት ቦታ የተመደበ
3 አርአያ ጌታቸው የፕሮዳክሽን ክፍልና ኦን ላይን ክፍል ሀላፊ አላግባብ ተቀትሮ ሶስት ደረጃ በድልድሉ እድገት ያገኘ
4 እስማኤል አረቦ ጥናትና ምርምር አላግባብ የተቀጠረ
5 ወርቁ ማሩ አድስ ዘመን ጋዜጣ አርታኢ አላግባብ የተቀጠረ
6 ሀይለ ገብርኤል ቢንያም አላግባብ የተቀጠረ በጥናትና ምርምር ክፍል የሚገኝ 7 ለገበያ ልማትና ለጥናትና ምርምር በሀላፊነት ቦታ የተመደቡ ወዘተ ይገኙበታል፡፡

ይህ ሁኔታ በመረጋገጡም የተወሰኑ የመዝገብ ቤት ሰራተኞች በዚህ ጉዳይ መዛግብት ደብዛ አጥፍተዋል ተብለው ከስራ ታግደዋል ይህ ሁኔታ ሲታይም የተፈጠረውን ስህተት በቀላሉ ማረም እየተቻለ አዲሱ አመራርና የቦርዱ ሊቀመንበር ለጉዳዩ የሰጡት ዝቅተኛ ትኩረት ተቁዋሙን የበለጠ አዘቅት ውስጥ እየከተተው ይገኛል፡፡

የተጠቀሰው ህገ ወጥ ድርጊት መስራያ ቤቱን በብዙ መልኩ ጎድቶታል
1 ያለ ውድድር ቅጥር መፈጸም የሺህ ኢትዮጵያውያንን የመቀጠር እድል አጨንግፎአል፡፡
2 ነባር ሰራተኞች ሊያገኙ የሚችሉትን የደረጃ እድገት አምክኖአል፡፡
3 ተወዳዳሪነት እንደያብብ አድርጎአል፡፡ ህገወጥነትን አጠናክሮአል፡፡

ከዚህም በላይ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው የመስራያ ቤቱ አመራርም በህግ ወጥ ቡድን እንዲሞላ አድርጎአል፡፡

ስለሆነም ለህግ ልእልና እንዲሁም ለፕሬስ እድገት የሚሙዋገት ከአቤቱታ አቅራቢዎች ጎን መቆም የሚገባቸው ሲሆን መንግስትም ችግሩን ተመልክቶ መፈትሄ ይስጠን እንላለን፡፡
የተቁዋሙ ሰራተኞች