የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየቀኑ ወደ አስመራ በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየቀኑ ወደ አስመራ በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ

የአማርኛ-ወሬዎች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየቀኑ ወደ አስመራ የሚያደርገውን በረራ በቀጣይ ሳምንት ሀምሌ 10 እንደሚጀምር አስታወቀ። አየር መንገዱ በቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ወደ አስመራ የሚያደርገውን በረራ በቦይንግ 787 እንደሚያደርግ ነው የተገለፀው።

አየር መንገዱ ወደ አስመራ የሚያደርገው በረራ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ የንግድ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተነግሯል።

ወደ አስመራ የሚደረገው በረራ ኤርትራ በኢንቨስትመንት፣ ንግድ፣ ቱሪዝም ተጠቃሚ እንድትሆን እና ሰፈውን የኤርትራ ዲያስፖራ ተደራሽ ለማድረግ ይረዳል ተብሏል።

በሁለቱ ሀገራት ሊኖር የሚችለውን ከፍተኛ የንግድ ግንኙነት መሰረት በማድረግም አየር መንገዱ በቅርቡ በየቀኑ በርካታ መደበኛ በረራዎች እንደሚያደርግ የገለፀ ሲሆን፥ የጭነት አገልግሎት በሚሰጡ አውሮፕላኖች በረራ እንደሚጀምርም ተቋሙ ይፋ አድርጓል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየቀኑ ወደ አስመራ በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ” የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየቀኑ ወደ አስመራ በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጉዞ በአስማራ አምስት ቀናት ቆይታ  ለሚያደርግ ተጓዥ ለደርሶ መልስ 7106 ብር እንደሚከፍል ተገልጿል።

ወደ አስመራ ለመጓዝ የሚያስችለውን ትኬት በሞባይል መተግበሪያ እና ከአየር መንገዱ ድረ-ገፅ ማግዛት እንደሚቻል የተገለፀ ሲሆን፥ በረራው 1ሰዓት ከ10 ደቂቃ ይፈጃል ተብሏል።

አየር መንገዱ ከ20 ዓመት በኋላ ወደ አስመራ የሚያደርገውን በረራ እንደሚጀምር ያስታወቀው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኤርትራ ባደረጉት ጉብኝት ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ ነው።

(በኤፍ.ቢ.ሲ)