የሀዋሳ ከንቲባና የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ስልጣን ለቀቁ

የሀዋሳ ከንቲባና የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ስልጣን ለቀቁ

የአማርኛ-ወሬዎች

የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ አዱላ እና የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸውን የደቡብ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽም ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ።

ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ አዱላ እና የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ በአካባቢው ለተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስና ተያይዞ ለተከሰቱት የህብረተሰብ ጉዳት ኃላፊነት በመውሰድን ከዛሬ ሰኔ 28 2010 ዓ.ም ጀምሮ በገዛ ፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው የለቀቁት።

በቦታቸው የሚተኩትን አመራሮችን በሚመለከት በተለመደው የድርጅቱ አስራር መሰረት የሚፈጸም መሆኑን የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽም ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

በሀዋሳ ከተማና አካባቢዋ ተከስቶ በነበረው ችግር የ10 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 89 ሰዎች ላይ ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት መድረሱ ይታወሳል።

እንዲሁም ግጭቱን ተከትሎ 2 ሺህ 500 ሰዎች ደግሞ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በደቡብ ክልል ግጭት ወደተከሰተባቸው አካባቢዎች በማቅናት ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ግጭት የተፈጠረባቸው አካባቢዎች ያሉ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ሀላፊነት ወስደው በፈቃዳቸው ስልጣን እንዲለቁ ጥሪ ማቅረባቸውም ይታወሳል።

(በኤፍ.ቢ.ሲ)