ኢትዮጵያ የኤርትራና የጂቡቲ ጉዳይ በሰላም እንዲፈታ ለመሳተፍ ጠየቀች

ኢትዮጵያ የኤርትራና የጂቡቲ ጉዳይ በሰላም እንዲፈታ ለመሳተፍ ጠየቀች
ኢትዮጵያ የኤርትራና የጂቡቲ ጉዳይ በሰላም እንዲፈታ ለመሳተፍ ጠየቀች

የኤርትራና የጂቡቲ ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ለመሳተፍ ኢትዮጵያ ዝግጅነቷን ገለጸች። ኢትዮጵያ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያሉ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ለመሳተፍ ዝግጁነቷን የገለጸችው የኤርትራና ሶማሊያ ጉዳይ የሚከታተለው ኮሚቴ ባለፉት ጊዚያት በኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሊያ ጉብኝት ካደረገ በኋላ የ120 ቀናት ሪፖርቱን በትናንትናው ዕለት ለጸጥታው ምክር ቤት ባቀረበበት ውቅት ነው ተብሏል።

በዚህም ኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ለ2 አስርት አመታት የዘለቀውን ቅራኔ በመፍታት በቀጠናው አካባቢ ሰላም እንዲሰፍን እየተሰራ ያለውን ተግባር ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ክብር ሊሰጠው እንደሚገባ የጸጥታው ምክር ቤት ገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በፈንጆቹ ሃምሌ 9 በሁለትዮሽ የሰላም አጋርነት ላይ ስምምነት መፈራረመቸውና በተመሳሳይ መልኩ የኤርትራና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት በሳለፍነው ቅዳሜ መፈራረማቸውን የኮሚቴው ሊቀመንበር የሆኑት አምባሳደር ኬራት ኡማሮቭ አድንቀዋል።

ከፈረንጆቹ መካቢት 14 አስከ ሃምሌ 30 ኮሚቴው ውጤታማ ስራ የሰራባቸው ጊዚያት ሲሆኑ፥ በኢትዮጵያ፣ ጂቡቲና ሶማሊያ ውይይቶች መካሄዳቸውንም ኮሚቴው አስታውቋል።

በቀጠናው ምልከታውን ያከሄደው ኮሚቴው አሚሶም ከሶመሊያ ከመውጣቱ በፊት ሶማሊያ የአካባቢውን ጸጥታና ደህንነት በረሷ አቅም ለመወጣት የሚያስችላት ደረጃ ላይ መድረስ እንዳለባት አመላክቷል።

አሁን ላይ ሶማሊያ የአካባቢውን የጸጥታና የደህንነት ጉዳይ በራሷ አቅም ለመቆጣጠር የምትችለበት ደረጃ ላይ ያለመድረሷ የተገለጸ ሲሆን፥ የአሚሶም ኃይል የቆይታ ጊዜውን እስከ ፈረንጆቹ ግንቦት 31፣ 2019 ማራዘሙ ነው የተገለጸው።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ አምባሳደ ተቀዳ አለሙ እንደገለጹት ላለፉት 20 ዓመታት በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከላል የዘለቀውን ቅራኔ በመፍታት አዲስ ምዕራፍ ተክፍቷል።

የሁለቱን ሀገራት የግጭት ምዕራፍ ከመዝጋት ባለፈም ሀገራቱ ለሁለቱ ሀገራት የህዝብ ለህዘብ ህዝብ ግንኑነት መሻሻልና ቀጣይነት ቁርጠኛ መሆናቸውን አስረድተዋል።

በዚህም ያለፉት 2 ሳምንታት ታሪካዊ መሆናቸውን የገለጹት አምባሳደር ተቀዳ ሁለቱ ሀገራት ለሰለማዊ ግንኙነታቸው የወሰዱት ቁርጠኝነት ለቀጠናው ሀገራት ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ ድርሻ ያለው ሲሆን፥ ለቀጠናው ሀገራትም በአርያነት የሚወሰድ ነው ብለዋል።

ለዚህም ከኢትዮጵያና ኤርትራ ሰላመዊ ግንኙነት በኋላ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሚስተር ሞሃመድ አብዱላሂ(ፋርማጆ) ከጥቂት ቀናት በፊት በኤረትራ ይፋዊ ጉብኝት ማድረጋቸው አንዱ ማሳያ መሆኑን ነው አምባሳደር ተቀዳ የተናገሩት።

ኢትዮጵያ የኤረትራና የጅቡቲ ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታና በቀጠናው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የበኩሏን ሚና እንደምትወጣም አስረድተዋል።

ለዚህም በማንኛውም መንገድ የሁለቱ ሀገራት ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ የሚፈታበትን ሁኔታ ለማገዝ ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን ነው የተናገሩት።

(በኤፍ ቢ ሲ)