ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በምዕራብ ጉጂ እና ጌዲዮ ዞን የተፈናቀሉ ዜጎችን ዛሬ ይጎበኛሉ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በምዕራብ ጉጂ እና ጌዲዮ ዞን የተፈናቀሉ ዜጎችን ዛሬ ይጎበኛሉ

የአማርኛ-ወሬዎች

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራ ከፍተኛ ልዑክ  በምዕራብ ጉጂ እና ጌዲዮ ዞን አካባቢ በተቀሰቀሰው ግጭት የተፈናቀሉ ዜጎችን እንደሚጎበኙ ተገለፀ።

በደቡብ ክልል በተለያዩ ቦታዎች በተከሰቱ  ግጭቶች  ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ እንደተቀንቀሳቀሰ መሆኑን  የክልሉ መንግስት ማስታወቁ ይታወሳል።

በክልሉ ከ770 ሺህ በላይ ዜጎች የተፈናቀሉ ሲሆን፥ ተፈናቃዮቹን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚያስችል መልኩ ከክልል እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ እየተሰራ ይገኛል ተብሏል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው ልዑክ ከኦሮሚያ እና ደቡብ ክልል የተውጣጣ ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተ ሲሆን፥ በተከሰተ ግጭት የተፈናቀሉ ዜጎችን ያወያያሉ ተብሎ ይጠባቃል።

ከተፈናቃሉ ዜጎች ጋር የሚካሄደው ውይይት በሰላም፣ ፀጥታ፣ በአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ እና በዘላቂ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ያተኮረ ነው ተብሏል።

በግጭቱ ምክንያት የተከሰተው አይነት አዳጋ በድጋሚ እንዳይከሰት ፣ የተፈናቀሉ ዜጎች በዘላቂነት ለማቋቋምና የተቀናጀ ድጋፍ ለማደረግ አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ተገልጿል።

(በኤፍ.ቢ.ሲ)